Addis Ababa administration to transfer 51,229 housing units to residents in Addis Ababa

Advertisements


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር 51229 የ20/80ና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ አስተላለፈ
በአዲስ አበባ የ13ኛ ዙር የ20/80 እና የ2ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ማውጣት ስነስርዓት በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ተካሂዷል፡፡
በስነስርዓቱም ላይ የመዲናው ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ለባለእድለኞች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ልማትን በጋራ መጠቀም ተገቢ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው፣ በቤቶቹ ግንባታ ከይዞታቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ለከፈሉት መስዋዕትነት ዋጋቸውን እንደሚያገኙም አመልክተዋል፡፡
በዚህም ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ልማት ሲባል ከመሬታቸው ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ያለእጣ ቤት እንዲሰጣቸው የከተማ አስተዳደሩ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስቴር አቶ ዣንጥራር አባይ በበኩላቸው በሀገሪቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የፍላጎቱና አቅርቦቱ ተመጣጣኝ ባይሆንም የዘርፉ ልማት ስኬታማ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በዚህም ልማት ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ውጤታማ እንደሆነች እንደማሳያ ጠቁመዋል፡፡
የጋራ መኖሪያ ቤቶች ልማት ለዜጎች የመጠለያ ቤት ከማቅረብ ባለፈ የስራ እድልና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንደፈጠረ ተናግረዋል አቶ ዣንጥራር፡፡
በቀጣይ የዘርፉ ልማት በመንግስት ብቻ መስራት ውጤታማ ስለማያደርግ የግሉን ዘርፍ ማሳተፍ ተገቢ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
ሚንስትሩ የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ፍትሃዊ እንዲሆንም ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በመሆን የማጣራት ስራ ተሰርቶ እንዲሻሻል መደረጉንም ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ነዋሪን የቤት ፍላጎት ለሟሟላት በየዓመቱ 470 ሺህ ቤቶች በመገንባት ለተጠቃሚ ማስተላለፍ እንደሚገባ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተገኘውቅ መረጃ ያመለክታል፡፡

Advertisements

NAIROBI 14 RIVERSIDE DUSIT D2 HOTEL ‘TERRORISM’ ATTACK

               በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ አልሻባብ የሽብር ጥቃት ፈፀመ በጥቃቱ 6 ሰዎች ተገድለዋል

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ዱሲት በተባለ ሆቴል ላይ በተኩስ እና በፍንዳታ ጥቃት መድረሱን ፖሊስ አመለከተ። ፍንዳው እና ተኩስ እንደተሰማ  ከሆቴሉ ሠራተኞች የተወሰኑት ሕይወታቸውን ለማዳን ሸሽተው መውጣታቸው ተገልጿል። መጠኑ ባልተገለፀው ፍንዳታ የሆቴሉ የተወሰኑ ክፍሎች በእሳት ሳይቃጠሉ እንዳልቀሩ የሚወጡ መረጃዎች እያመለከቱ ሲሆን  ጭስ ከሕንፃዎች ሲወጣ መመልከቱን  የጀርመን የዜና ወኪል ዘግቧል። ዴይሊ ኔሽን በበኩሉ ባወጣው መረጃ ደግሞ ቆስለው ሆስፒታል ህክምና ሲደረግላቸው ከነበሩት መካከል 6 ሰዎች ሞተዋል ሲል ዘግቧል

። ናይሮቢ በሚገኘው ዱሲት ሆቴል ስለደረሰው የፍንዳታ እና የተኩስ ጥቃት የሚያመለክቱ ዘገባዎች ከስፍራው መውጣቱን ተከትሎም ሶማሊያ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ፅንፈኛ ቡድን አልሸባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል።  ሮይተርስ ከመቅዲሾ እንደዘገበው  ደግሞ የቡድኑ ቃል አቀባይ ጥቃቱ እንደሚቀጥልና ፈጻሚውም አልሸባብ መሆኑን አረጋግጠዋል። ጥቃቱን ፈፃሚዎቹ ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ  ሆቴሉ ውስጥ የመሸጉ ሲሆን መሽገዋል በተባሉት ጥቃት አድራሾች እና በፖሊስ መካከል ፍጥጫው ቀጥሏል።

Addis Ababa ቦሌ ክፍለ ከተማ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል የሁለት ባልደረቦቹን ህይወት አጠፋ

images
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 24 ፣ 2011 በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በመጠጥ ሀይል ተገፋፍቶ በባልደረቦቹ ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል እንደተናገሩት፥ የፌደራል ፖሊስ አባሉ በባልደረቦቹ ላይ በፈፀመው ጥቃትም ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ህይወት አልፏል።
ፖሊስ ጥቃቱን ለማስቆም በወሰደው እርምጃም ጥቃቱን የፈፀመው የፌደራል ፖሊስ አባል ህይወቱ ማለፉን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅም በስፍራው ተስተጓጉሎ የነበረው የትራፊክ እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ሁኔታቸው መመለሳቸውን ገልፀዋል።