Abebe gelaw ጋዜጠኛ አበበ ገላው ለአቶ በቀለ ገርባ መልስ ሰጠ

ደኢህዴን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ 23 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱን አሰናበተ

s-1

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2011 የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ድርጅታዊ ጉባዔ 23 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱን በክብር አሰናበተ።

ደኢህዴን በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ባለው ጉባዔ ነው ነባር አመራሮቹን በክብር ያሰናበተው።

በዚህም መሰረት፦

 1. አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ

2.አቶ ሽፈራው ሽጉጤ

 1. አቶ ሲራጅ ፈጌሳ
 2. አምባሳደር ተሾመ ቶጋ

 3. አቶ ተክለወለድ አጥናፉ

 4. አቶ ሳኒ ረዲ

 5. አቶ ታገሰ ጫፎ

 6. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

 7. ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም

 8. አቶ ደበበ አበራ

 9. አቶ መኩሪያ ሀይሌ

 10. አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ

 11. አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ

 12. አቶ ተመስገን ጥላሁን

 13. አቶ ወዶ ኦጦ

 14. አቶ ያዕቆብ ያላ

 15. አቶ ሰለሞን ተስፋዬ

 16. አቶ ፀጋዬ ማሞ

 17. አቶ ንጋቱ ዳንሳ

 18. አቶ አድማስ አንጎ

 19. አቶ ኑረዲን ሀሰን

 20. አቶ ሞሎካ ወንድሙ

 21. አቶ አብቶ አልቶ ናቸው ከማእከላዊ ኮሚቴው በክብር የተሰናበቱት።

ከማእከላዊ ኮሚቴ የተሰናበቱት አባላት ከ17 እስክ 15 ዓመታት በተለያየ የሀላፊነት ደረጃ ያገለገሉ መሆኑም ተገልጿል።

ጉባዔው በተጨማሪም ከድርጅቱ ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን አቶ ካሚል አህመድን በክብር አሰናብቷል።

እንዲሁም የደኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ እስከ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በእግድ እንዲቆዩ አድርጓቸው የነበሩ አባላትንም ድርጅታዊ ጉባዔው አሰናብቷል።

በዚህም መሰረት፦

 1. ወይዘሮ አማረች ኤርሚያስ

 2. አቶ ሳሙኤል ደምሴ

 3. ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ከድርጅቱ ተሰናብተዋል።

Ethiopian Civil Aviation Authority / ዘጠኝ የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

40112681_1124452567718086_844728339506659328_n9 የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሰሞኑን የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል በሚል ወንጀል የጠረጠራቸውን 9 የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

ፖሊስ በእነሱ ብቻ ሊሰራ የሚችለውን  የኢትዮጵያ አየር መንገድየአየር ትራፊክ ቁጥጥር የሥራ ዕንቅስቃሴ ለማስተጓጎል ሕገወጥ የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል በሚል ወንጀል በመጠርጠር እንደያዛቸው ገልጿል፡፡

የሀገርን ገፅታ ማበላሸት ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚው ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ እንዲያደርግ በማሰብ ወንጀሉን ፈፅመዋል የሚለውም ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ካደረጉ ምክንያቶች ተጠቃሽ ነው ብሏል ኮሚሽኑ ፡፡

ፖሊስ የመብት ጥያቄ ቢኖራቸው እንኳ እየሰሩ መጠየቅ የሚችሉበትን መፍትሔ መከተል ሲችሉ ሆነ ብለው የአየር መንገዱን የስራ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል የደመወዛቸውን አንድ ሺህ እጥፍ  ማለትም 1000 % ጭማሬ  መጠየቃቸው  አግባብ ባለመሆኑና ሆነ ተብሎ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለመጉዳት አስበው መንቀሳቀሳቸው በመረጋገጡ በህግ ሊጠየቁ ችለዋል ብሏል ፡፡

የአገር ኅልውናና ድንበር ቋሚ ናቸው ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ
የአገር ኅልውናና ድንበር ቋሚ ናቸው ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ነሐሴ 6 ቀን 2010 ዓ/ም ( August 12, 2018 )

የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ላለፉት 10 ዓመታት በተለይ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ከሱዳን ጋር በሚያዋስነው ድንበር አስመልክቶ፤ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከኢትዮጵያ ሕዝብ በስተጀርባ ያደረገውን ሴራና ደባ በቅርብ እየተከታተለ ለባለ ጉዳዩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ እያደረገ በማጋለጥ የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ ይታወቃል።

በተለያዩ ጊዚያቶች እንደገለጽነው፤ ሕወሓት ከሱዳን ጋር የሚደራደረው የድንበር ስምምነት ኢትዮጵያ ባልተቀበለችው የቅኝ ግዛት ሠነድ በማስረጃነት በጠቀም በመሆኑ፤ የአገራችንን ጥቅም አሳልፎ የሰጠና ሉዓሏዊነቷን ያስደፈረ የአገር ክህደት ተግባር ነው።
ይህ ርዝመቱ ክ 1600 ኪሎ ሜትር የጎን ስፋቱ ድግሞ 30 እስከ 40 ኪሌ ሜትር የሆነው ለም የድንበር መሬት በተደጋጋሚ በመሬት ላይ ችካል ለመትክል ያደረጉት ጥረት በሕዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ ሳይሳካ እንሆ እስክዛሬ መቅረቱ ይታወቃል።

ይሁን እንጅ፣ ምንም እንኳን የ1600 ኪሎ ሜትሩ የድንበር መሬት አስምረው ለሱዳን ለማስረከብ ባይሳካላችውም ከሱዳን ጋር ከሚያዋስኑት በጎንደር ክ/ሃገር ለም የእርሻ መሬቶች መካከል የተወስኑ መሬቶችን መስጠታችው በተደጋጋሚ ተገልጾ ነበር። የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ይህንኑ ክሱዳን ጋር የተደረገውን የድንበር ስምምነት ለማግኝት ለበርካታ ዓመታት ጥረት ሲይደርግ ቆይቶአል።

ይህን የአገርን ጥቅምና ሉዓላዊነትን አሳልፎ የሚሰጠውን የድንበር ስምምነት ማን ነው ኢትዮጵያን ወክሎ የፈረመው የሚለው ጥያቄ በዛን ወቅት በሕዝቡ በስፋት በተነሳበት ጊዜ፣ በወቅቱ የአማራው ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን እንደሆኑ ተደርጎ ህዝቡ እንዲያምንና በዋናነት በሠነድ ላይ የፈረመው ስው እንዳይታውቅ ከፍተኛ ጥረት ተደርጉ ነበር። በዚህም መሠረት፣ አቶ ደመቀ መኮንን እንደፈረሙ በብዙ ሕዝብ ዘንድ እንዲታመን ተደርጎ ቆይቶአል።

እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ፤ ከብዙ ድካምና ጥረት በኋላ 3 የእርሻ መሬቶችን አሳልፎ ለሱዳን ለማስረክብ የተፈረመው የመግባቢይ ሠነድ በኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ እጅ ሊገባ ችሏል። ይህ 8 አንቀጾች ያሉት ሠነድ የሚያረጋግጠው ኢትዮጵያን ወክለው የፈረሙት ሕወሓት እንዳስወራው አቶ ደመቀ መኮንን ሳይሆኑ፤ የፈረሙት አቶ አባይ ፀሐየ መሆናችውን በግልፅ ያሳያል። ሱዳንን ወክለው የፈረሙት ደግሞ የሱዳን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ናቸው። አቶ ደመቀ መኮንን ምንም ባልዋሉበትና ባላደረጉት ወንጀል ያለአግባብ ሆን ተብሎ እንዲወራና የአማራ ክልል ባለሥልጣን መሬቱን አሳልፎ ለሱዳን እንዳስረከበ ተደርጎ እንዲወስድና የወንጀሉ ዋና አካል የሆኑትን ሕወሓት እና አባይ ፀሐየ ከደሙ ንጹህ ለማድረግ ሆን ተብሎ የተፈመ ሴራ ነበር። ይህ የኢትዮጽያን ጥቅም አሳልፎ የሠጠ የመግባቢይ ስነድ የኢትዮጽያ ህዝብ እንድያውቀው ከዚህ መግለጫ ጋር በአባሪነት አቅርበናል።

ይህ በአቶ አባይ ፀሐየ የተፈረመው የመግባቢያ ሠነድ ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች መካከል፤

በመግባብያ ሠነዱ ላይ በግልጽ የተቀመጡ 3 የእርሻ ቦታዎች አሉ። ከነዚህ መካከል ሁለቱ (2) ማለትም፥ በታማራት ኩባንያ እና ሃሰን ሞሐመድ ቶም የሚባሉት “በውሳኔው መሠረት በአስቸኳይ” ለሱዳን መንግሥት ተላልፈው እንዲሰጡ ይላል። ሦስተኛው (3ኛው) ከማል ኡረኢቢ እርሻን በሚመለከት ግን “ኮሚቴው በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲያገኝለት” በማለት ያሳስባል። እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው ቦታዎቹ የሱዳን ኩባንያ ስያሜ እንዲሰጣቸው መደረጉን ነው። ሠነዱ እንደሚያረጋግጠው ሁለቱም ፈራሚ ባለስልጣናት በቦታው ድረስ መገኝታችው ይገልፃል።

ይህ የመግባብያ ሠነድ ኢትዮጵያና ሱዳን እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ1902 እና 1907 የተደረጉትን ስምምነቶች እንደተቀበለች አድርጎ ለማቅረብ ሞክሮል። የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴና በርካታ የታሪክና የሕግ ምሑራን ውድቅ ያደረጉትን ሠነድ በማስረጃነት ማቅረቡ ህውሐት ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳደረገው ሁሉ ህጋዊ ባልሆነ ሰነድ ለማስፈፅም የታቀደ ለመሆኑ ያረጋግጣል። በተደጋጋሚ እንደተገለጸው፤ ቀደምት የኢትዮጵያ መንግሥታት ከላይ የሰፈሩትን ስምምነቶች አስመልክተውም ሆነ የሱዳን መንግሥት በየዘመኑ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ያልተቀበሉ መሆናቸው ግልጽ ነው።

ሌላው በጣም የሚደንቀውና የሴራው እምብርት የሆነው ጉዳይ ደግሞ፤ እነዚህ የተጠቀሱት ስፍራዎች የሚገኙት ሕወሓት በፈጠረው በአማራ ክልል ውስጥ መሆናቸው እየታወቀ ስምምነቱ የፈረመው ግን የትላንቱ የሕወሓት ከፍተኛ ሹም አቶ አባይ ፀሐየ መሆናቸው ነው።
ገና ከጥዋቱ ጀምሮ ኢትዮጵያዊነትንና የኢትዮጵያን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ለ27 ዓመታት ከፍተኛ ግፍና መከራ በሕዝብና በአገር ላይ የፈጸመው የሕወሓት አመራር፤ ለሕዝብና ለአገር በእውነት ቆመው የታገሉትን ሁሉ ያለ ጥፋታቸው ጥፋተኛ በማስመሰል ያለ ስማችው ስም እየሰጠ በእሥር እንዳሰቃየ ሁሉ፤ በራሱ መንግስት መዋቅር ውስጥ የሚሰሩትን ጭምር ያላደረጉትን አደረጉ በማለት ሲያስር መቆየቱ የአደባባይ ምሰጢር ነው። በዚህ የሕወሓት መሰሪ ተግባር እንዲጠቁ የተደረጉት አቶ ደመቀ መኮንንም ይዋል ይደር እንጅ ይሄው እውነቱ ዛሬ በአደባባይ ይፋ ለመሆን በቃ። የህወሐት ሹሞች ገና ጫካ እያሉ የገቡት ቃል እነዚህ ከላይ ተጠቀሱትን 3 የእርሻ መሬቶች ብቻ ሳይሆን፤ 1600 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለውን የድንበር መሬት ለማስረከብ እንደነበርና ይህንንም ስምምነት ገና ከጅምሩ ሕወሓትን በመወከል ከሱዳን ጋር ይነጋገሩ የነበሩት አበይ ፀሐየ እንደነበሩ አቶ ገብረመድህን አርአያ በዛን ጊዜ የህወሐት አባል የነበሩ የዚህ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ አባል ለኢትዮጵያ ሕዝብ መግለጻቸው ይታወሳል።

ይህ የድንበር ጉዳይ በህወሓት አመራር ሰጪነት ከተፈጠሩ ውስብስብ የአገራችን ችግሮች አንዱ ቢሆንም ችግሩ ትላንት የተፈጠረ ተብሎ ብቻ የማይታለፍ፣ ዛሬም ከባድ በሆነ ሁኔታ የዜጎችን ነፍስ እየቀጠፈ ያለ ጉዳይ በመሆኑ የድንበር ጉዳይ ኮሚቴው ከመቼውም ጊዜ በላይ ሁኔታውን በትኩረት እየተከታተለው ይገኛል። በተለይ በጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው የለውጥ ኃይል በኢትዬጵያ ፖለቲካ አይነተኛ የለውጥ አመራር መስጠቱንና መላው ህዝብ በተስፋ አብሯችው መሰለፉን ያልወደዱት ቡድኖች አስቀድመው ከአገር በስተጀርባ የጎነጎኑትን የፖለቲካ ሸፍጥ በመጠቀም ሂደቱን ለማደናቀፍና መሪወቹን ከህዝብ ጋር ላማጋጨት ባለፉት ሁለት ወራት በድንበሩ አካባቢ ግልፅ ጦርነት እንዲከፈት አድርገዋል። በዚህም የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት አልፏል። ይህ የብዙ ወገኖቻችንን ህይወት እየቀጠፈ ያለው ችግር ትኩረት የሚሻና መፍትሄ የሚያስፈልገው አብይ ጉዳይ መሆኑን በአንክሮ ለመግለፅ እንውዳለን።

ዛሬ ከፍተኛ የህዝብ ፍቅርና ድጋፍ በተጉናፀፉ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር በዶ/ር አብይ አህመድና ከሳቸው ጋር ባሉት የለውጥ ኃይሎች በፈጠሩት አገራዊ ስሜት የተነሳ፤ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ እንደገና የገነኑበት ወቅት ውስጥ ስለምንገኝ፤ ከጎረቤት አገራት ጋር በሰላም፣በመከባበርና በጋራ አብሮ በተለያዩ ዘርፎች በመሥራት ላይ የአተኮረ ግንኙነት የሚፈጠርበት እንጅ፤ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ የማይሰጥበት ወቅት ላይ ነን ብለን እናምናለን። አያይዘንም ይህ ኢትዮጽያንና ኢትዮጽያዊነትን ከፍ ያደረገ ለውጥ በዲሞክራሲ ድል አድራጊነት እንዲጠናቀቅ መላው የኢትዮጽያ ህዝብ ተገቢ ድጋፍ ማድረግ እንደሚኖርብን እንገነዘባለን። የጋራችን የሆነችውን ውድ አገራች ኢትዮጽያን ህልውና ዛሬም እንደ ጥንቱ አባቶቻችን ነቅትን የመጠበቅ የትውልድ አደራ አለብን።

የኢትዮጵያ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት በቆራጥ ልጆቿ የከበራል!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ለ20 ዓመታት ተዘግቶ በቆየው የኤርትራ ኤምባሲ ውስጥ ምን ተገኘ?

በ1990 የድንበር ጦርነቱ ሲቀሰቀስ አዲስ አበባ ውስጥ ለሁለት አሰርት ዓመታት ተዘግቶ ከቆየው የኤርትራ ኤምባሲ ልዩ ልዩ ክፍሎች የኤርትራ ባለስልጣናት በተገኙበት ሲከፈት ክፍሎቹ ውስጥ ፣ የቤት ውስጥ እቃዎች እና የተለያዩ መጠጦች ባሉበት ተገኝተዋል።በግቢው ውስጥ ደግሞ የቀድሞው ባለስልጣናት ይጠቀሙባቸው የነበሩ መኪናዎች ከቦታቸው ሳይንቀሳቀሱ በአቧራ እንደተሸፈኑ ተገኝተዋል

ጦርነቱ በ1992 ቢያበቃም ያለ ጦርነትና ያለ ሰላም የሁለቱ አገሮች ግንኙነት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ ሻክሮ ቆይቶ ነበር።
አዲሱ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ለእርቅና ሰላም ፍለጋ ወደ ኤርትራ መጓዛቸውን ተከትሎ በሁለቱም አገሮች ሰላም በመፈጠሩና ሁለቱም አገሮች ኤምባሲዎቻቸውን ዳግም ለመክፈት በተፈራረሙት ቃል መሰረት ስምምነታቸውን ተግባራዊ ለማድረግ በተመሳሳይ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ተከትሎ ነው ዛሬ ሀምሌ 9 2010 ዓ.ም ኤምባሲው መልሶ የተከፈተው።

እናም ኤምባሲው ሲከፈት እነዚህን ጨምሮ በርካታ የኤምባሲው ንብረቶች ምንም ሳይነኩ አቧራ እንደለበሱ በዚህ ሁኔታ ተገኝተዋል

5

4

ለ20 ዓመታት ተዘግቶ በቆየው የኤርትራ ኤምባሲ ውስጥ ምን ተገኘ?

3
6

እነዚህ ፎቶግራፎች የኤርትራ ኤምባሲ ዛሬ ሲከፈት በቢቢሲ የተነሱ ናቸው።

 Dr Debretsion Gebremichael Speech

“ሀገሪቱ አጣብቂኝ ውስጥ ነች” ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

FB_IMG_1530630983062
በዛሬው ዕለት የትግራይ ምክትል ርእሰ መስተዳድር እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከትግራይ ከያንያን እና የሚድያ ባለሙያዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ ውለዋል።

ዶክተር ደብረፅዮን ባቀረቡት የውይይት መነሻ ሀሳብ ላይ ሀገራችን አሁን ያለችበት ሁኔታ ቆም ብሎ ማሰብ የሚያስፈልግበት ነው ብለዋል።

ኢህአዴግ በተሃድሶ ግዜው ያስቀመጣቸው የለውጥ መንገዶች ከሞላ ጎደል መልካም ነገር የታየባቸው ቢሆኑም በጣም በርከት ያሉ ጉዳዮች ደግሞ በተፈለጉበት መንገድ አለመሄዳቸው አብራርተዋል።

ዶክተሩ እንዳሉት “ለምሳሌ በእስር የነበሩ ወንጀለኞች የሚፈቱበት አቅጣጫ ያስቀመጥን ቢሆንም የፀጥታ ሀይል የገደለ ይፈታ ግን አላልንም። ምክንያቱም ህገ ወጥነት ነው” ብለዋል።

በተሃድሶው ጊዜ ከአራቱ የኢህዴግ አባል ድርጅቶች ተሃድሶው በሚገባ እና ለትግል በሚጋብዝ መልኩ የመራው ህወሓት መሆኑ ገልፀው ግምገማው ደግመው እንድያዩት የተደረጉ ኦሆዴዶች እንደነበሩም ገልፀዋል።

ዶክተር ደብረፅዮን በማብራርያቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን እለቃለሁ ማለታቸውን ተከትሎ በኦሆዴድ የታየ የሀላፊነት መቀያየር ሩጫ፤ ከፍተኛ የስልጣን ጥማትን የምያሳይ እና አሁን እየታየ ላለው ችግር መነሻ መሆኑም ገልፀዋል።

በተለይም አሁን አሁን እየታዩ ያሉት የድጋፍ ሰለማዊ ሰልፎች ህገ መንግስቱ እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ የሚፃረሩ መልእክቶች እየተላለፉበት ያሉ መሆኑም ገልፀዋል። ህገወጥ መልእክቶቹም መቆም እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ዶክተሩ በንግግራቸው በማነኛውም የአገራችን ህዝብ ያለ የመለወጥ እና የመልማት ፍላጎት በማነኛውም መልኩ መደናቀፍ የለበትም። እሳቸው እንዳሉት ከአማራም፣ ከኦሮሞም፣ ከደቡብም፣ ከሶማሌም፣ ከዐፋርም ወዘተ አብሮ መስራት የምያስችል ዲሞክራስያዊ ሀይል ስላለ ነገሮች የሚስተካከሉበት መንገድ ማፈላለግ ይገባል። ጥንቃዌም ያስፈልጋል።

የተሃድሶ መድረኩ በስርዓቱ እና በተቀመጠለት አቅጣጫ ባለመሄዱ አሁን ሀገራችን አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለችም አስምረውበታል።

ድምፂ ወያነ!

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ነዳጅ የማውጣት ስራውን ለማስቆም የቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገለፀ !

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር  ነዳጅ የማውጣት ስራውን ለማስቆም  የቻለውን  ሁሉ እንደሚያደርግ ገለፀ !

ኢትዮጵያ በሙከራ ደረጃ  በሶማሌ ክልል ነዳጅ ማውጣት መጀመሯን ተከትሎ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ተግባሩን እንደሚቃወመው አስታወቀ። ነዳጅ የማውጣት ስራውን ለማስቆምም የቻሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ የግንባሩ ቃል አቀባይ አብዱልቃድር ሃሳን አዳኒ ለቢቢሲ ሶማልኛ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል ።

ቃል አቀባይ አብዱልቃድር ሃሳን ሲናገሩ ”የሶማሌ ክልል ህዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነት እስካላገኙ ድረስና ለረጅም ጊዜ የቆየው የሶማሌ ህዝብና የኢትዮጵያ መንግስት አለመግባባት እስካልተፈታ ድረስ፤ የነዳጅ ማውጣት ስራው የህዝቡን ሃብት ያለአግባብ እንደመጠቀም ነው” ብለዋል

የኢትዮጵያ ፖለቲካና ኢኮኖሚ አካል ስላልሆንን፤ ምንም አይነት ባህላዊ ቁርኝት የለንም፤ ስለዚህ የሶማሌ ህዝብን የተፈጥሮ ሃብትና መሬት ለሌላው ጥቅም ማዋል የማንቀበለው ነው በማለት ግንባሩ አቋሙን ገልጿል።

”መሬታችን በሃይል የተወሰደብን ሲሆን፤ እሱን ለማስመለስና የተጀመረውን ነዳጅ የማውጣት ስራ ለማስቆም የምንችለውን ነገሩ ሁሉ እናደርጋለን። ምክንያቱም በክልሉ ያለው ሃብት ለክልሉ ህዝቦች ብቻ ነው መሆን ያለበት፤ ማንም ሊጠቀመው አይችልም ሲሉ አክለው ገልፀዋል፡፡

ምንም እንኳን ግንባሩ በይፋ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባይነጋገርም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ  ለሁሉም ቡድኖች ያቀረቡትን የውይይት ሃሳብ ግን በበጎ ጎኑ እንደሚመለከተው ገልጿል።

አቶ አብዱልቀድር አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የግጭት ዋና ምንጭ የሆኑት ጉዳዮች ላይ በማተኮር አዲስ ምዕራፍ የመጀመር አጋጣሚው እንዳላቸውም ጨምረው ተናግረዋል። የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ኤርትራን ዋና መቀመጫው ያደረገ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት አስመራ አማጺዎችን ትደግፋለች በማለት ሲከስ ነበር፤ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባርን አሸባሪ ብሎ ብሎ የፈረጀው እንደነበር የሚታወቅ ነው  ።

ይሁንና በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስት ከለቀቃቸው የፖለቲካ እስረኞች መካከል የግንባሩ አመራሮችም የሚገኙበት ቢሆንም  የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ግን  ከ1976 ጀምሮ አሁንም የሶማሌ ራስ ገዝ አስተዳደር መኖር አለበት ብሎ የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ነው ፡፡

ከዚህ ቀደም በ2001 ዓ.ም ግንባሩ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ የቻይናው ነዳጅ አፈላላጊ ድርጅት ላይ  ጥቃት ፈጽሞ 74 ኢትዮጵያውያንና ዘጠኝ ቻይናውያን መግደሉም የሚታወስ ነው ፡፡

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ከአመራሮቹ አብዛኛዎቹ አባላት በአሁኑ ሰአት በውጪ ሃገራት የሚገኙ ሲሆን ግንባሩ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ 34 ዓመታትን ማስቆጠሩ ይነገርለታል ፡፡