የህወሓት ስትራተጂክ ግምገማ የአንድ ቤተሰብ ስልጣን አረጋግጦ ወጣ!!!

የህወሓት ስትራተጂክ ግምገማ የኣንድ ቤተሰብ ስልጣን ኣረጋግጦ ወጣ!!!

ከአስገደ ገብረስላሴ (መቀሌ )

December 1, 2017

የህወሓት የ5 ሳምንት ግምገማ ውጤቱ የኣንድ ቤተሰብ እና የኣንድ መንደር ሙሶኞች የስልጣን ስብስብ የመዘበሩት ሀብት ዋስትና እንደሚሰጥ ኣድር ሰርተውት ወጡ ።

ኣንድ ኣንድ የዋሇች ወገኖች ኣባይ ወልዱ ኣንድ ደረጃ ዝቅ ማለቱ ደብረጽዮንና ፈትለወርቅ ( ሞጆሪኖ )ኣንድ ኣንድ ደረጃ መውጣውጣታቸው ፣ኣዜብ መሰፍን ከሁሉም ደረጃ ማእከላይ ኮሚቴ መታገዳ ፣ በየነ ሞክሩ ዝቅ ማለቱ ፣ለኣዲስ ኣለም ባሌማ ማስጠንቅያ መሰጠቱ፣ ሌሎቹም ቢወረፉ ሲሰማ በትግራይ ክልልና ህዝቦቻ ብሎም በሀገር ደረጃ ያሉ ዘርፈቡዙ ችግሮች ሊፈቱ እንደሚችሉ እና በሀገራችን ያሉ የሙሱና ፣ምዝበራ ፣የዘረኝነት የቢሄር ፣የጎጥ ግጭቶች ደም መፋሰስ መሰረታዊ ለውጥ እንደሚመጣ 26 ኣመትን ሙሉ ስር የሰደደ የፍትህ እጦት ፣ድህነት ማህበራዊ ችግሮች ፣የህግ በላይነት ስደት ኣባይ ወልዱ ከስራኣስፈጻሚ መባረር ሁሉም በሀገራችን ያሉ ሁሉም ችግሮች ኣብረው እንደተሸኙ ኣድርጎ በማር የተለወሰ ኣዋጅ በማስተጋባት ከእንግዲህ ስርኣቱ ለኢትዮጱያ ህዝቦች ምቾት ኣልጋ በኣልጋ ንሮ እንደሚያመጣ ዲሞክራሲ እና የዜጎች ሰብኣዊ መብት እንደተረጋገጠ ።ኣፈና ጸረዲሞክራሲ ያልተመጣጠነ የሀብት ክፍፍል እንደሚኖር ኣድርገው የሚመለከቱ ወገኖች የሚደናገሩ ኣሉ ።

ኣንድ ኣንድ ተጠቃሚ ሰዎች ኣሁን ለመጣው የቤተሰብ ቡዱን ትስስር ያላቸው ተላላኪ ሰዎች እስከቀበሌ በኔት ወርክ ተደራጅተው ለወረሩት ሃብትና በዜጎች ላይ የፈጸሙት ወንጀል እንዳይ ጋለጡ ዋስትና በማግኜታቸው ።ከእንግዲህ ወዲህ ሰላምና መረጋጋት እንደሚሰፍን ለማሳመን ቤት ለቤት የሚሽለኮለኩ እንቅልፍ ኣጥተው የሚያድሩ ኣሉ ።

በሌላ በኩል በመላው ሀገራችን ያለው እጅግ ቡዙ የተወሳሰበ ችግር ኣሁን 5 ሳምንታት በጨረሰ የጥቂት የህወሓት የኣማራር ስብስብ በተደረገ ስብሰባ እና ኣደናጋሪ ኣዋጅ መፍትሄ ሊመጣ ኣይችልም ።እነደዚህ ኣይነት ስብሰባ ፣የተቀናበረ የውሼት ኣዋጅና ማስተጋባት 26 ኣመት ሙሉ ጆራችን ያደንቆረ ፣ ያሰለቸን በመሆኑ ፣ የነዚህ የቤተሰብ ስብስብም ለሀገራችን እና ለህዝባችን ከመጤፍም የሚያህል ለውጥ ኣያመጣም በማለት የስብሰባ ወጤት ወጤት ኮንነውታል ምክንያቱም ሁሉም የሚሉን ሀቅነት የለውምና ።

ይህ ኣባባል ትክክል ነው ። ምክንያቱም የህወሓት የቤተሰብ ኣማራር ቡዱን ከበረሀ ጀምሮ በየጊዜው የውሼት ኣጀንዳ በመፈብረክ ወይ በመክፈት ብዙሀኑ በመዳናገር በቡዙሀኑ ተቀባይነት የሌላቸው ኣሽኮሮች እየመለመለ በኣማራሩ ውስጥ እያስገባ ይዞት የመጣ ባህሪ ነው ።ለዚሁ ለመረጋገጫ ያህል በ1969 / 1972 /1977 / 1982 /1985 / 1993 / ዓ / ም ከዛ በኃላም የመተካካት ተሀድሶ ፣በቅርቡ ደግሞ የሙሱና ዘመቻ በማለት በዬጊዜው በራሱ ውስጣዊ ብልሽት እና ጸረ ዲሞክራሲ ተፈጥሮ ከቤተሰብ የኣመራር ቡዱን ውጭ የሆኑ ፣ወይ በኣስተሳሰብ ቅንነታቸው የታወቀ ቡቁ ሙሁራን በሀገራዊና አለም ኣቀፋዊ ኣመለካከታቸው የመጠቁ ወገኖች ምክንያት እየፈጠረ እጅግ ቡዙ ወገኖች እያጠፋ ፣ከኑራቸው ከሰራቸው እያፋናቀለ ፣ ለእሱር ለሞት ፣ ለስደት እየዳረገ ፣ዜጎች እርስ በእርሳቸው እያጋጨ ኣላስፈላጊ ግጭቶች እልቂት የዜጎች ሀብት ማውደም መውረር እንዲደርስ ኣድርገዋል ።

የሀገራችን ሀብት በባለስልጣናትና በቤተሰቦቻቸው በሸሪኮቻቸው ወራሪ ለነሱ ኣቀባዮች ባለሀብቶች በሆኑ ሌቦች በሞኖፖል በመያዝ በተጨማሪ የሀገራችን ቁልፊ የኢኮኖሚ ኣውታር የሆኑ የሀብት ክምችት ወይ ካፒታል በህወሓት ኢህኣደግ እና ተላላኪ ኣጋሮቻቸው ፓርቲዎች እጅ ተይዘው የውጭ ምንዛሪ መከማቻ በማድረግ የሀገራችን የውጭ ምንዛሪ ( ዶላር ፣ፓውንድ ፣ የሌሎች ኣገሮች ውድ የሆኑ ገንዘብ ) በመዛቅ ባገር ውስጥና በውጭ በማካማቸት ፣ ልጆቻቸው በሀገራች ዶላር መዝብረው በሁሉም የሀያላን መንግስታት ልጆቻቸው በማስተማር እች ኣገር በዝብዘዋታል ።

ልጆቻቸው የምራባውያን ዜግነት ይዘው እንዲያድጉ ሚስቶቻቸው ኣመሪካ ፣እንግሊዝ ፣ ጀርመን ወዘተ እየላኩ ስፍር ቁጥር የሌለው የሀገራችን የገንዘብ ካዝና እየወረሩ እንዲወልዱ ያደርጋሉ ።

ይህ የሚያሳየን እነዚህ ሰዎች የሚገፋቸው የተቀናጀ የሙሁሩ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ማህበረሰብ ድክመት ነው እንጅ እነዚህ ፍጡራን ኣስቀድመው ከ20 ኣመት በፊት በሚሞሩት ስርኣት መተማመን እንዳልነበራቸው ኣንድቀን ቁርጥ ቀን ስትመጣ እንደመንግስቱ ሀይለማሪያም የሚፈረጡጡ መሆናቸው ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ እንደመጡ ኣንድ መረጋገጫ ነጥብ ነው።

የተከበራቹ የኢትዮጱያ ህዝቦች በተለይ ደግሞ በሁሉም ይዞቱ ውስጠ ወይራ (ተንኮል ) የህወሓት ኣማራር ተጠቂ የሆንከው የትግራይ ህዝብ ባለፉት 5 ሳምንታት የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ የውሼት ግምገማና የውሼት የግምገማው ውጤት ኣዋጅ ሲያንሳፍፉህ የሰነበቱ ። እጅጉን ኣግራሚ የሆነ ከላይ እንደዘረዘርኩት ሀቂ ኣገራችን በመሪዎች የሙሱና የሀብት ወረራ እና ምዝበራ በስብሰው እያሉ በዚሁ የ5 ሳምንት ግምገማና ሂስ ግለሂስ ስለሙሶኞች ኣንድም ቃል ትንፍሽ ኣላሉም ። ይህ የሙሶኞች ኣጀንዳ ኣንስተው ሙሶኞች ኣለመምታታቸው ደግሞ የግምገማቸው ውጤት ውሀ ቢወግጡት እቡጭ ያደርገዋል። እኔ የገረመኝ የኣባይወልዱ ኣማራር እጅግ ኣስቀያሚ እንደነበረ እምነቴ ቢሆንም ፣ በሙሱና ከነዘር መንዘራቸው ቢሊዬነር ፣ሚሊዮነር የሆኑ በቢሊዮን ገንዘብ የተሰራ ህንጻዎች በባለቤትነት የያዙ ሳይነኩ መታለፋቸው ነው ። በመሆኑም ይህ የህወሓ ማ / ኮ ግምገማ እንዳለፉ የ26 ኣመት የውሼት ግምገማዎች ውጤት ኣልባ ኣታለይ መሆኑ ያራጋግጣል ።

እጅጉ የሚያሳዝነው ግን በመጭው ሳምንታትየሚደረገው የባኣዴን ፣የኦሆዴድ ፣የዴኸደን ፣የኣጋር ፓርቲው ግምገማ ከዚሁ የህወሓት የውሼት ስትራተጅካዊ ግምገማ ጥልቅ ተሞክሮ ቀስመው ሊያጭበረቡሩን (እንደጌቶቻቸው ሊያንሳፉፉን ) ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸው ነው ።

ከአስገደ ገብረስላሴ  (መቀሌ )

01/12 / 2017